የሴት ልጅ ግርዛት ምንድን ነው?
የሴት ልጅ ግርዛት ወይም የብልት ግርዛት በብዙ የአፍሪካ ሀገራት እና በአንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ እና እስያ ሀገራት የተለመደ ባህል ነው። ብዙውን ጊዜ እስከ 15 ዓመት ዕድሜ ባላቸው ሴት ልጆች ላይ ይከናወናል።
በጣም የተለመደው የግርዛት አይነት የቂንጥር ውጫዊ ክፍል ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በማስወገድ የሚደረግ ግርዛት ነው። በአንዳንድ አገሮች የሴት ብልት ጠባብ እንዲሆን የብልት ከንፈር አያይዞ መስፋት የተለመደ ነው።
በኖርዌይ ሁሉም አይነት የብልት ግርዛት የተከለከለ ነው። የሴቶች ግርዛት በሚፈጸምባቸው አብዛኞቹ አገሮችም ታግዷል።
የጤና እርዳታ
ከተገረዙ እና ህመም ወይም ሌላ ችግር ካለብዎ ስለዚህ ጉዳይ ለመነጋገር እና እርዳታ ለማግኘት ማነጋገር የሚችሉት የጤና አገልግሎቶች አሉ፥
- የእርስዎ ቋሚ ሃኪም
- በጤና ጣቢያ እና በትምህርት ቤት ጤና አገልግሎት ውስጥ የሚገኝ የጤና ነርስ
- ከእርግዝና ጋር በተያያዘ በጤና ጣቢያ ያሉ አዋላጅ የጤና ባለሙያዎች
ዶክተሮች፣ የጤና ነርሶች እና አዋላጆች አስፈላጊ ከሆነ በሆስፒታል ውስጥ ወደሚገኝ የሴቶች ክሊኒክ፣ የማህፀን ሕክምና ክፍል ወይም የህጻናት ክሊኒክ ሊመሩዎት ይችላሉ።
ጥልቅ እውቀት ባላቸው ባለሙያዎች የሚሰጥ ሕክምና
በሴት ልጅ ግርዛት ላይ ጥልቅ እውቀት ያለው የሕክምና አገልግሎት በስድስት ሆስፒታሎች ውስጥ ይሰጣል። እዚያ እንዲላኩ መጠየቅ ይችላሉ አብዛኛዎቹን ግን እራስዎ ያለ ሪፈራል ማነጋገር ይችላሉ። የእነዚህ ሆስፒታሎች ዝርዝር በዚህ ገጽ መጨረሻ ላይ ይገኛል።
ወጪዎች እና የምስጢርነት ግዴታ
- የጤና እንክብካቤ በጤና ጣቢያ ነፃ ነው።
- የግል ሀኪሞ ጋር እና በሆስፒታል ውስጥ የእርሶን ድርሻ መክፈል አለቦት።
- የጤና ባለሙያዎች ሚስጥርን የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው ።
በሴቶች ግርዛት ምክንያት የጤና ችግሮች
የሴት ግርዛት ለብዙ የረጅም ጊዜ ህመሞች እና ውስብስብ ችግሮች ሊያስከትል ይችላል።
ለምሳሌ፥
- የሆድ ቁርጠት
- በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት ህመም
- የሚያሠቃይ እና ዘገምተኛ ሽንት
- ፈሳሽ መጨመር
- ከወር አበባ ጋር የተያያዙ ችግሮች
- ቂንጥርን ወይም የብልት ከንፈር አካባቢ ላይ እባጭ
የተሰፋውን መክፈቻ ቀዶ ጥገና እና ሌሎች ሕክምናዎች
ግርዛቱ የሴት ብልት አካል ጠባብ እንዲሆን ካደረገ ስፌቱን መክፈት ብዙውን ጊዜ ብዙ የህመም ስሜቶችን ለማስወገድ ይረዳል። ይህ በብልት አካባቢ በሚሰጥ ማደንዣ ሊደረግ የሚችል ትንሽ ቀዶ ጥገና ሊፈታ ይችላል።
የወሲብ ህይወት ከመጀመርዎ በፊት ይህን ማድረግ ጥሩ ነው። እርጉዝ ከሆኑ፣ በወሊድ ጊዜ የተሰፋውን መክፈት ብዙውን ጊዜ ይመከራል፣ ነገር ግን በእርግዝና ወቅትም እንዲሁ ማድረግ ይቻላል።
ሌላ ዓይነት ግርዛት ከሆነ ያሎት ለህመም እና ለሌሎች በሽታዎች እርዳታ ሊያገኙ ይችላሉ።
ልዩ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች መረጃ
በሚከተሉት ሆስፒታል የሚገኙ የሴቶች ክሊኒኮች ልዩ እንክብካቤ ለሚያስፈልጋቸው ሴቶች ልዩ የሕክምና አገልግሎት ይሰጣሉ ፥
ትሮምሶ
Universitetssykehuset i Nord-Norge
በዚህ ስልክ ቁጥር ወደ ሴቶች ክሊኒክ ይደውሉ 77 62 64 50
በርገን
Haukeland Universitetssykehus
በዚህ ስልክ ቁጥር ወደ ሴቶች ክሊኒክ ይደውሉ 55 97 42 36
ትሮንድሃይም
የጥቃት ክፍልን ለማግኘት በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ 72 57 12 12
ኦስሎ
Oslo Universitetssykehus Ullevål
በዚህ ስልክ ቁጥር ወደ ሴቶች ክሊኒክ ይደውሉ 22 11 98 44
ድራመን
ስልክ ቁጥር 32 80 30 00/ 03525
የማዋለጃ ክሊኒክን ይጠይቁ። እርጉዝ እና እርጉዝ ያልሆኑትንም ይቀበላሉ።
ክርስቲያንሳንድ
Sørlandet sykehus HF, Kristiansand
በዚህ ስልክ ቁጥር ወደ ሴቶች ክሊኒክ ይደውሉ 38 07 30 70
ከዶክተር፣ ከጤና ነርስ ወይም ከአዋላጅ የጤና ባለሙያ ሪፈራል ያስፈልግዎታል